Admin2
Sat, 06/13/2026 - 15:41
3ኛው ዙር የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ውድድር፣ ዓውደ-ርዕይና የፓናል ውይይት እየተካሔደ ነው
" የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን የሳይንስ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ማዕከል እናድርግ"በሚል መሪ ሀሳብ የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ውድድርና የፓናል ውይይት በቡታጅራ ከተማ እየተካሔደ ነው
የፈጠራ ስራ ውድድር አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት በዘርፉ የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ ጥረት እንደሚያጠናክር ተመላክቷል።
በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ሌሎች ከክልል እና ከዞኖች የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩ እለቱን አስመልክቶ የተዘጋጀ የመወያያ ጽሁፍ ቀርቦ ምክክር እንደሚደረግበት ይጠበቃል።