Skip to main content
Zena111

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ 3ኛውን ዙር የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ውድድርና ዓውደ-ርዕይ በቡታጅራ ከተማ መርቀው ለዕይታ ክፍት አደረጉ

(ሆሳዕና፣ሰኔ 5/2018) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 3ኛው ዙር የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ውድድርና ዓውደ-ርዕይ በቡታጅራ ከተማ ተመርቆ ለዕይታ ክፍት ሆነ

ክልሉን የሳይንስ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ማዕከል እናድርግ በሚል መሪ ሀሳብ ለሁለት ተከታታይ አመታት የፈጠራ ስራ ውድድር አውደ ርዕይ እየተካሔደ ነው።

በ3ኛው ዙር የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ውድድርና ዓውደ-ርዕይ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ ተወዳዳሪዎች ልዩ ሽልማት ይበረከትላቸዋል።

በአውደ ርዕዩ ልዩ ልዩ የፈጠራ ስራዎች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለህዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ተመላክቷል።

ይህን የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች ውድድር አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት የክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ የሳይንስ ኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ፣የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተር ፕራይዝ ልማት ቢሮ እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ በትብብር አዘጋጅተውታል።

በመርሐ ግብሩ የፌደራል፣የክልል እና የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በተስፋዬ መኮንን