Admin2
Wed, 06/03/2026 - 12:31
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በወራቤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ስራ አስጀመሩ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ስራ አስጀመሩ። በማዕከሉ በ6 ተቋማት 20 አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑም ተመላክቷል። በምረቃ መርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የክልል እና የስልጤ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።