Admin2
Tue, 12/23/2025 - 17:47
የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ1ኛ ግማሽ ዓመት ስራዎች ክትትልና ድጋፍ ስራ ማድረግ ጀመረ። ወራቤ: ታህሳስ/2018 ዓ/ም የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በዞንና በልዩ ወረዳ ሳኢቴ መዋቅሮች የ2018_በጀት_ዓመት የ1ኛ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግ ቡድን በማሰማራት እየገመገመ ይገኛል። በክትትልና ድጋፍ ስራ የታዩ ዋና ዋና ተግባራት:- የሪፎርም ትግበራና እና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም አተገባበር; በየመዋቅሩና ተቋማት የዲጂታላይዜሽን ትግበራ እና የኢኖቬሽን/ፈጠራ ስራዎች ድጋፍ ስራዎች; እንዲሁም ሌሎችንም ተግባራት በማካተት በጥንካሬ የተፈፀሙትን አጠናክሮ በማስቀጠል በሂደቱ መሻሻል የሚገባቸውን ተግባራት በመገምገም የሚያርም ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።