Skip to main content
zena70

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር የተቋሙን ዌብሳይት ማበልፀግ፣ሎጎ የማስተዋወቅ ስራ እና የተቋሙን የጥናትና ምርምር መረጃ መሰብሰቢያ ሶፍትዌር ርክክብ ስራ አከናወነ። በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የመግቢያ ንግግር ያረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ እንዳሉት ሥልጠናው ከክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር መሠረታዊ የሶፍትዌር አጠቃቀምና አስተዳደር ላይ ዕውቀትና ክህሎት እንዲኖር ዕድል የሚፈጥር ነው ብሏል። በቀጣይም በተግባር የተደገፈ ሥልጠና እንደሚሰጥም ኃላፊው ገልፆዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የአመራር አካዳሚው ዋና ዳሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱን ጨምሮ የዳሬክተሩ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች፣የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሸን ቢሮ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፏል።