Skip to main content
zen57
በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተማሪዎችን በስፔስ ሳይንስና በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተመለከተ።‎ ‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ድጋፋዊ የክትትል ቡድን በጉራጌ ዞንና በቀቤና ልዩ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያና ፅ/ቤት ተገኝቶ በተቋሙ የተግባር እንቅስቃሴን ተመልክቷል። ‎ ‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽ ቴክኖሎጂ ቢሮ በምክትል ሀላፊ ማዕረግ የቢሮው አማካሪ በአቶ አብድራህማን አህመድ የተመራው ድጋፋዊ የክትትል ቡድኑ በሰጠው አስተያየት በጉራጌ ዞንና በልዩ ወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት መደበኛና የንቅናቄ ተግባራትን የመራበት አግባብ አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል ይጠበቅበታል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። ‎ ‎በተመሳሳይም በክረምት የበጎ ፍቃድ ተግባር ለማከናወን በዘርፉ እቅድ ታቅዶ ወደተግባር የተገባበት መንገድ በመገምገም በወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኮሌጅ ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን ለመጠቀም በስፔስ ሳይንስና በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እየወሰዱ ያሉበትን አግባብ ተመልክተዋል ። ‎ ‎አክለውም በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በዘርፉ ዜጎችን ለማስጠቀም እቅድ በማቀድ ወደተግባር መገባቱንና ተግባሩ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ።