Admin2
Tue, 08/05/2025 - 19:05

አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የግብ ስምምነት ተፈራረሙ
(ሆሳዕና፣ሐምሌ 29/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ በተገኙበት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ የግብ ስምምነት ላይ ከሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ተፈራርመዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ከጤና ፣ከትምህርት ፣ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ከሴቶችና ህጻናት ጉዳይ፣ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና፣ከወጣቶችና ስፖርት፣ከባህልና ቱሪዝም፣ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ፣ከአመራር አካዳሚ፣ከሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂቢሮዎች ጋር የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።