
መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመከታተል ወደወልቅዬ እና ዋቸሞ ተመድበው ለመጡት ሰልጣኞች ገለጻ እና የኢትዮ-ኮደር ስልጠና ተሰጠ።
በትምህርት ሚኒስቴርና በክልሉ ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት ከነገ ጀምሮ በሚሰጠው ልዩ የክረምት ስልጠና 5 ሺህ 31 የሁለተኛ ደረጃ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠናውን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
ከክልሉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡት መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች በዋቸሞ እና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች ነው ስልጠናውን የሚወስዱት። ሰልጣኞች የአቅም ግንባታ ስልጠናውን ለመከታተል ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርስቲ በዛሬው ዕለት ገብተዋል።
በዚህ ወቅት እንደገለፁት በትምህርት ሚኒስቴርና በክልሉ ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት ከነገ ጀምሮ በሚሰጠው ልዩ የክረምት ስልጠና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 5 ሺህ 31 የሁለተኛ ደረጃ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠናውን ይወስዳሉ። ስልጠናው በክልሉ በዋቸሞ እና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ የገለጹት ኃላፊው ይህም ለትምህርት ጥራት መሻሻል ጉልህ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ክፍተኛ የሶፍት ዌር አበልፃጊ አቶ መንሱር ሀምዛ በስልጠና መረሀግብሩ ላይ አጠቃላይ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ሂደት ምንነት ላይ ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አያይዝውም ሰልጣኞች በዲጂታሉ አለም ተወዳዳሪ መሆን ይቻል ዘንድ በየኢትዮ-ኮደር ፕሮግራም ላይ ስልጠና ያልጀመሩ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች እንዲጀምሩና የጅመሩም አጠናክረው እንዲቀጥሉና ሁሉም በትኩረት መሰልጠን ይገባቸዋል ያሉት ባለሙያው የተቀመጡ 4 የስልጠና ደረጃዎችን በማጠናቀቅ ሰርቲፋይ እንዲሆን አሳስበዋል።