Skip to main content
zena59

የህክምና መሳሪያዎች እና የመድሀኒት ስርጭት አስተዳደር ስርዓትን የሚያዘምን የመረጃ ቋት ሶፍት ዌር በማልማት ወደ ስራ መግባቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር የመረጃ ቋት ሶፍት ዌር በማልማት ርክክብ ማድረጉን አስታዉቋል የጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊና የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሀብቴ ገ/ሚካኤል የሶፍትዌር ርክክቡን ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት የህክምና መሳሪያዎች እና የመድሀኒት ስርጭት አስተዳደር ስርዓትን የሚያዘምን የመረጃ ቋት ሶፍት ዌር በማልማት ወደ ስራ መገባቱን ገልፀዋል የመረጃ ቋት በሶፍትዌር መታገዙ የመረጃ ፍሰቱን ቀላልና ግልፅ ለማድረግ ወሳኝ ስለመሆኑ የጠቆሙት አቶ ሀብቴ ወረቀት አልባ አሰራርን ለማጠናከርና ፍትሀዊ የግብአት ስርጭትን በማጎልበት የህብረተሰቡን የህክምና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው አክለዋል ። ከዚህ ቀደም ለጤና ተቋማት የህክምና ግብዓት በወረቀት ርክክብ በማድረግ እንደሚሰራጭ የገለፁት አቶ ሀብቴ ይህ ስርዓት ግብአትን በተገቢዉ ለማስተዳደር እና ለመቆጣጠር አዳጋች በመሆኑ የሶፍትዌር መልማቱ ይህን ችግር በዘላቂነት እንደሚቀርፍ አመላክዋል በየጤና ተቋማት የሚሰራጨው መድሀኒት የመጠቀሚያ ግዜያቸውን በአግባቡ ለመለየትና ለመቆጣጠር ሶፍትዌር መልማቱ አስፈላጊ ስለመሆኑ ያነሱት ም/ሀላፊው ከጤና ሚኒስቴር እና ከአጋር ድርጅቶች የሚመጡ የህክምና ግብአቶችን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የመረጃ ቋትን በመጠቀም በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ በተገቢው ማየትና መከታተል ያስችለዋል ብለዋል። ከዚህ ቀደም የህክምና ግብአቶች ለጤና ተቋማት በሚሰራጩበት ወቅት የመረጃ ክፍተት በመኖሩ ደግመን በመላክ ከፍትሀዊነት አንፃር ጥያቄ ሲፈጥር እንደነበር የገለፁት አቶ ሀብቴ ይህ ሶፍትዌር መልማቱ የመረጃ ክፍተቶችን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀርፍ ጠቁመዋል አቶ ዳርጊቾ አህመድ የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው የህክምና ቁሳቁሶችን ለታችኛዉ መዋቅር በአግባቡ ለማሰራጨት ሶፍትዌር መልማቱ ፋይዳዉ የጎላ ስለመሆኑ ጠቅሰዉ የመረጃ ቋቱ ትክክለኛ እና አስተማማኝ መረጃን በቀላሉ እንድናገኝ ይረዳናል ብለዋል። የክልሉ ጤና ቢሮ ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የመረጃ ቋት ሶፍት ዌር በማልማት ርክክብ አድርገዋል ።