Skip to main content
zena57

በየደረጃው የሚሰጠውን አገልግሎት ውጤታማ ለማድረግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መጠቀም በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፥መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ አስታወቀ። ሀምሌ10/2017ቢሮው አሰራሩን ለማዘመን ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑም ተመላክቷል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፥መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ ከቶ ዳዊት ኃይሉ እንደገለጹት በየደረጃው የሚሰጠውን አገልግሎት ውጤታማ ለማድረግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መጠቀም በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል። የተቋሙን አቅም በቴክኖሎጂ ለማጎልበት ድህረ-ገጽ በልማት ለህዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት ግልጽነት እና ተአማኒነት ያላቸውን መረጃዎች ተደራሽ ለማድረግ ሁሉን አቀፍ ጥረት እየተደረገ ስለመሆኑ ኃላፊው አመላክተዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ በበኩላቸው ቢሮው ከተለያዩ የክልሉ መንግስት ተቋማት ጋር ባደረገው ግንኙነት 38 ድህረ-ገጾችን ማልማት መቻሉን ገልጸዋል። የክልሉ ውሀ ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማዘመን የቴክኖሎጂ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን አቶ ሰላሙ አብራርተዋል።