Skip to main content
zena55

የክልሉ የቱሪዝም ጸጋ በአግባቡ ለመጠቀም በቴክኖሎጂ የታገዘ የቱሪዝም ስራ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የበለጸገው "የክልሉ የቱሪስት መስህቦች መረጃ ማስተዳደሪያ ሲስተም" እርክክብ ተደረገ። የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ምክትል እና የቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኑሪ ከድር እንደገለጹት በክልሉ በርካታ ባህላዊ ፣ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ የቱሪዝም መስህቦች ያሉ ሲሆን የእነዚህ መስህቦች መረጃ በአግባቡ ተሰንደው ቱሪስቶች በቀላሉ እንዲያገኙዋቸው የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው። በተለይም አገልገሎት ሰጪ ተቋሟት እና የቱሪዝም መስህቦች መረጃ የማደራጀት ስራ አንዱ ሲሆን የቱሪስት መስህቦች መረጃ ማስተዳደሪያ ሲስተም ደግሞ ለዚህ ተግባር የጎላ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። የክልሉ የቱሪዝም ጸጋዎች በመለየት ፣በማልማትና በማስተዋወቅ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ያሉ ቱሪስቶች እንዲጎበኙ ተደርጓል ያሉት ኃላፊው በዘርፉ የሚገኘው ገቢ ማሳደግ ተችሏል። የጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፖርክ ከነበረበት ችግር በማውጣት ጥሩ መነቃቃት የተፈጠረ መሆኑና በአሁን ሰአትም በውስጡ ያሉ የዱር እንስሳቶች ጨምሮ ጥቅል ያሉ ሀብቶች ምዝገባ እየተደረ መሆኑ ተናግረዋል። የክልሉ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች መሰረተ ልማት ለማሟላት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር እየተሰራ ሲሆን ለአብነትም ከክልሉ መንገዶች ባለስልጣን የውል ስምምነት መደረጉ አስታውሰዋል። ቱሪስቶች በክልሉ ሰፊ የጉብኝት ጊዜ እንዲኖራቸው በሆቴል ኢንቨስትመንቱ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸው በብቃት ላይ ተመስርቶ እንዲሄድ መመሪያ ማጽደቅ መቻሉ ተናግሯል። አቶ ኑሪ አክለውም መስህቦቻችን በጎግል ማፕ ውሴጥ እንዲገቡ ከቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢኒስቲትዩት ጋር ስምምነት ተደርጓል ብለዋል። የክልሉ የቱሪዝም ሀብቶችና ጸጋዎች በማወቅ በመለየት እና በጥናት በማስደገፍ ቱሪዝሙ ለስራ እድል ፈጠራ ያለው አበርክቶ ከፍ እንዲል ተሰርቷል። አሁን ባለንበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን የቱሪዝም ስራን ከቴክኖሎጂ ጋር አስተሳስሮ መስራት ጠቀሜታው ከፍተኛ ሲሆን ቱሪስቶች የቱሪዝም ስፍራዎች ፣አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ሌሎች የሚፈልጉዋቸው አካባቢዎች በቀላሉ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል ብለዋል አቶ ኑሪ። የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ እንዳሉት በዘርፉ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንና ለአብነትም የባህልና ቱሪዝም ኩነትና አጠቃላይ የተቋሙ ስራ የሚያዘምን ዳታ ቤዝ ማልማት መቻሉ አስታውሰዋል። ተቋማት ወደ ዲጂታላዜሽን ለመጓዝ የሚያደርጉት ጥረት የሚያግዝ ፣ ተገልጋዮች የሚፈለጉዋቸው መረጃዎች ሳይንገላቱ ፣ወጪ ሳያወጡ የፈለጉት አገልግሎት በቀላሉ የሚያገኙበት ሲስተም ነው ብለዋል። የቱሪዝም ተቋሙ የያዛቸው እራዮችን በቀላሉ ለማሳካት በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ መስራት ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ከበደ ዌብሳይት በማልማት ፣ድህረገጽ በማበልጸግ ፣ዳታ ቤዞችና አንድሮይድ አፕሊኬሽኖችን በመጫን በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልጸዋል። የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንዳሉት መምሪያው ዘመኑን የሚሙጥኑ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስራዎች በመስራት ጥራት ያለው ፣ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥ እያተደረገ ነው ብለዋል።