Skip to main content
zena53

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በ2.8 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገዙ የተለያዩ እቃዎችን ድጋፍ አደረገ። ‎ ‎ድጋፉ እንተርኔት ኬብል፣ ሜንቴናንስ ቱልኪት፣ ድሪል ማሽን፣ የኮምፒዩተር አክስሰሪ፣ ኔትወርክ ቱልኪትን ጨምሮ የተለያዩ ለጥገና፣ለስልጠና፣ለእድሳት እና ለኢንኩቤሽን ማዕከል ማሻሻያ የሚዉል እቃዎችን ያካተተ ሲሆን በክልሉ ለሚገኙ ዞኖችና ልዩ ወዳዎች ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያዎችና ጽህፈት ቤቶች ተበርክቷል። ‎ ‎በረክክቡ ወቅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ ድጋፉ ክልሉን የሳይንስ ፣ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ ታስቦ እየተሰራ ያለውን ስራ በማጠናከር ከዳር ለማድረስ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። ‎ ‎ ቢሮው ሁሉም መዋቅሮች ተግባራቸውን በቴክኖሎጂ ታግዘው ውጤታማ ስራዎችን እንዲሰሩ ለማስቻል ለባለሙያዎች በተለያዩ የስራ መስኮች በነበሩ መሠረተ-ልማት የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና መስጠቱን አቶ ከበደ ገልጸዋል። ‎ ‎ አክለውም የድጋፉ የዲጂታል ስልጠና ማዕከላትን ለማጠናከርና መሠረተ-ልማቱን በወቅታዊ ቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ እንደሆነም ጠቁመዋል። ‎ ‎ የተቋሙን ግቦች ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመፈጸም ቢሮው በቀጣይም የተለያዩ ድጋፍችን የሚያደርግ መሆኑን በመግለፅ ለተሻለ ውጤታማነት በትጋት መስራት ይጠበቃል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ‎ ‎ድጋፍ የተደረገላቸው አካላት በበኩላቸው ቢሮው ያደረገላቸው ድጋፍ የዲጂታል ማዕከላትን ለመቋቋም፣ ለማሻሻል እና ለማጠናከር ብሎም በየደረጃው ለሚሰራው ስራ ጉልህ አበርክቶ ያለው መሆኑን ተናግረዋል።