Skip to main content
zena45

ብቃት ያለው እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ዜጋ ለመፍጠር በኢትዮ ኮደርስ የተገኘውን እድል መጠቀም እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) አሳሰቡ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) እንደገለጹት ብቃት ያለው እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ዜጋ ለመፍጠር በኢትዮ ኮደርስ የተገኘውን እድል መጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋል። በየደረጃው ያለው አመራር የኢትዮ ኮደርስ የስልጠና መርሐ ግብር ስኬታማ እንዲሆን በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። መምህራን፣የጤና ባለሙያዎች፣የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት፣ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን አጠናቀው በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ዜጎች በስልጠናው በንቃት ሊሳተፉ ይገባል ብለዋል። በተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚገኙ አመራሮች፣ሰራተኞች ፣ወጣቶች፣ሴቶች እና በልዩ ልዩ የሙያ መስክ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በስልጠናው መሳተፍ እንዳለባቸው ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል። በኢትዮ ኮደርስ የስልጠና መርሐ ግብር መሳተፍ ብቻ ግብ አይደለም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ስልጠናውን በብቃት አጠናቆ ሰርተፍኬት ማግኘት የሚቻልበትን መርህ መከተል ተገቢ ስለመሆኑም አብራርተዋል።