
ስልጠናው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ያለንን ሙያዊ አቅም የሚያጎለብትና ክፍተቶቻችንን በመለየት በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንድንችል አጋዥ ነው - ሰልጣኞች። ስልጠናው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ያለንን ሙያዊ አቅም የሚያጎለብትና ክፍተቶቻችንን በመለየት በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንድንችል የሚያደርግ ነው ሲሉ ሰልጣኞች ተናገሩ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከክልልሉ ከሁሉም ዞኖች፤ ልዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣቱ የኢኮቴ ከፍተኛ ባለሙያዎች በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች የሚሰጠው የአድቫንስድ ቴክኒካል ስልጠና እንደቀጠለ ነው። ከክልሉ ከተለያዩ መዋቅሮች ለተወጣጡ የኢኮቴ ከፍተኛ ባለሙያዎች ለ30 ተከታታይ ቀናት በአራት ዙር ለአንድ መቶ አስራ ሁለት ሰልጣኞች ለመስጠት ታስቦ ከሳምንት በፊት የተጀመረው ስልጠና እንደቀጠለ ነው። በስልጠናው እያሉ ያነጋገርናቸው አንዳንድ ባለሙያዎች እንደገለፁት በሶፍትዌር ልማት ማበልጸግ፣በቢሮ ማሽን ጥገናና ዕድሳት፣በኔትወርክ ልማትና አስተዳደር ዙሪያ እውቀት እየቀሰሙ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅማችንን የሚያጎለብትና ክፍተቶቻችንን በመለየት በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያግዘን ነው ብለዋል ። ስልጠናው ዲጅታል ቴክኖሎጂ ለመገንባት በሚደረገ ጥረት የሚታዩ የክህሎት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ሰልጣኞች ተናግረዋል። ሰልጠኞች ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ እንደመሆናቸው መጠን እርስ በርስ ልምድና ተሞክሮ ለመለዋወጥ ዕድል የፈጠረ እንደሆነም አክለዋል።