Admin2
Thu, 04/17/2025 - 22:09

የፈጠራ ስራ ውድድርና ኤግዚቤሽን የእስካሁን አፈፃፀም አበረታች መሆኑ ተገለፀ። የፈጠራ ስራ ውድድርና ኤግዚቤሽን የእስካሁን አፈፃፀም አበረታች መሆኑን የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኋላፊ አቶ ሠላሙ አማዶ ገለጹ። ቢሯችን ከትምህርትና ከኢንተርፕራይዝና ስራ ዕድል ፈጠራ ሴክተሮች በጋራ በቅንጅት በማስፈፀሚያ ዕቅዱ መሠረት በት/ት ቤቶች; በወረዳ; በልዩ ወረዳ እና በዞን ደረጃ የፈጠራ ስራ ውድድርና ኤግዚቤሽን አፈፃፀም የተሻለ መሆኑን የቢሯችን ኋላፊ ገልጸው አመስግነዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኋላፊው በቀሪ ጊዜ ቀሪ መዋቅሮች በማስፈጸሚያ ዕቅዱ መሠረት በየደረጃው የፈጠራ ስራ ውድድርና ኤግዚቤሽን በማስኬድ እንድታጠናቅቁ አሳስበዋል።