Skip to main content
zena36

የጥንቃቄ መልዕክት ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች❗️ የኢንተርኔት አጠቃቀም በየቀኑ እየጨመረ በሄደበት በዚህ ዘመን፣ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ስጋቶችም እየተስፋፉ ነው። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በቅርቡ በርካታ አደገኛ የኢንተርኔት አድራሻዎችን (URLs) መርምሮ፣ እነዚህ አድራሻዎች ለሀገራችን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በይበልጥ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች አካዉንቶችን በመንጠቅን ከፍተኛ ስጋት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አረጋግጧል። ከተለያዩ አካላት በቴሌግራም የሚደርሱን ሊንኮች በርካታ አደጋዎችን የሚይዙ ሲሆን የሚከተሉት አደጋዎች በዋናነት ይገኙበታል፡ 👉የግል መረጃ መጠለፍ:- እንደ የባንክ መለያ ወይም የይለፍ ቃል ያሉ መረጃዎችን መሰረቅ፤ 👉የማልዌር ስርጭት:- ስልኮችን ወይም ኮምፒውተሮችን የሚጎዱ ቫይረሶች፤ 👉ማጭበርበሪያ:- ተጠቃሚዎችን በሀሰተኛ ተስፋዎች (እንደ ውርርድ ወይም ኢንቨስትመንት) መታለል፤ በመሆኑም ማኅበረሰቡ በቴሌግራም አማካኝነት የሚላኩለትን አጠራጣሪ ሊንኮች ከመክፈት እንዲቆጠብ እያሳሰብን፤ ሰሞኑን በቴሌግራም ከሚላኩና በፍጹም ልንከፍታቸዉ ከማይገቡ ሊንኮች መካከል የሚከተሉት ከታች በምስሉ ያሰፈርናቸዉ ይገኙበታል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቴሌግራማችን አጠራጣሪ የሆኑ ሊንኮች ካጋጠመን ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሚከተሉት አድራሻዎች ማሳወቅ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ • e-mail: ethiocert@insa.gov.et • ነጻ የስልክ መስመር፡ 933