
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር ) የማህበራዊ ክላስተር ሴክተሮች የዕቅድ አፈጻጸም በጽ/ቤታቸው እየገመገሙ ነው ሆሳዕና፣መጋቢት 15፣2017፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የማህበራዊ ክላስተር መስሪያ ቤቶች አመራሮች እና ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የክላስተሩ ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገሙ ነው። ከአመራሩ እና ከየሴክተሩ ማኔጅመንት አባላት ጋር የተጀመረዉ የዉይይት መድረክ ተግባራት እንዴት ተመሩ?፣ በቅንጅት የመሥራት ሁኔታዎች ፣ የተግባራት ክትትልና ድጋፍ ሁኔታ፣ ተግባራት መሬት ላይ በትክክል የሚገኙ ስለመሆናቸው የተረጋገጠበት አግባብ ላይ የሚያተኩር መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር/ ) ጠቁመዋል ። መድረኩ የተግባራት አፈፃፀምና ዉጤታማነትን፣ የህብረተሰብ ተጠቃማነትን ከማሳደግን አኳያ ፤ የአመራርና የመላዉ ሠራተኛ ቅንጅት፣ በተመለከቱና ቀጣይ ትኩረቶችን ሚሹ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑንም ርዕሰ መስተዴድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር/ ) አመልክተዋል ። በዛሬዉ ዕለት ወራቤ ማዕከል የሚገኙ የማህበራዊ ክላስተር መስሪያ ቤቶች ማለትም የትምህርት፣ የጤና ፣ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት፣የሣይንስና ኢንፎርሜሽን፣ የሴቶችና ህፃናት ቢሮዎች ተግባራት የእሰከ አሁን አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነዉ። በተመሳሳይ ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ከዱራሜ እና ከቡታጅራ ክላስተር መስሪያ ቤቶች አመራሮችና ማኔጅመንት አባላት ጋር ቀደም ባሉት ቀናት ዉይይት ማካሄዳቸው ይታወሳል ።