Skip to main content
zena29

የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የ8 ወራት ዋና ዋና ተግባር አፈፃፀም በማነጅመንት ገመገመ። በየዘርፉ የእስካሁን አፈፃፀም ከዕቅድ አኳያ በጥንካሬ፣ መሻሻል በሚገባቸውና ቀጣይ ትኪረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ሪፖርት ቀርቦ መገምገም ተችሏል። በመድረኩ የተገኙት የቢሮ ኋላፊ አቶ ሠላሙ አማዶ የእስካሁን ተግባር አፈፃፀም አበረታችና መልካም መሆኑን አንስተው በቀሪ ጊዜያት ተረባርበን የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ አክለው አንስተዋል። የማነጅመንት አባላትም በዝርዝር አንስተው ገምግመዋል።