
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ እና የክልሉ ጤና ቢሮ እንደ ተቋም የመረጃ ስርዓቱን ለማዘመን እና ጊዜውን የዋጀ መረጃን ለማደራጀት ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ እና ከጉራጌ ዞን ሳይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመቀናጀት የሲስተም ልማት ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል። ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በወራቤ ከተማ በጋራ በሲስተም ልማት ስራ የተከናወኑ አፈጻጻም ግምገማ አድርጎል። ውይይት የተደረገባቸው ሲስተሞች የሴቶች ልማት ህብረት መረጀ መደረጃ ዳታቤዝ ሲስተም እና የጤና አገልግሎት መገልገያ ቁሳቁስ አስተዳደር ዳታቤዝ ሲስተም ሲሆን በማልማት ሂደት ላይ ያሉ ሁለቱም ሲስተሞች ሲጠናቀቁ የተቋማቱን አሠራር ዲጂታላይዝ ለመድረግ እና ቀልጣፈ አሠራር ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለው እና በዚህ ሂደት ውስጥ የተቋማት የመረጃና የአሠራር ስርዓት የበለጠ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን። በተጨማሪም የመረጃ ልውውጥ ስራዓት በዳታቤዝ ሲስተም ኦንላይን በመሆኑ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ የአሠራር ስርዓቶችን በጤናው ዘርፍ እና በሴቶች ልማት ህብረት ዘርፍ በማህበረሰቡ መካከል ያለውን የመረጃ ልውውጥ በአካል ይካሄድ ከነበረበት በይነ-መረብ/ በዲጂታላይዘሽን በማሸጋገር በጣም ፈጠን ፣ወጪ ቆጣቢ እና ደህንነቱ የተጠበቀ አስተማማኝ እንዲሆን ከማድረጉም በተጨማሪ ወቅታዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ወዳ ተቀናጀ ና አካታች ዲጂታል ኢኮኖሚ የሚደረግ ጉዞ እውን እንዲሆን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ወይም በማላመድና ነባር ቴክኖሎጂን በማሻሻል እና በአገልግሎት ላይ በማዋል ህብረተሰቡ ከዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል ከተቋማት ጋር በቅንጅትና በትብብር መስራቱ ወሳኝ እና አስፈላጊ መሆኑን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊ እና የኢኮቴ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሸሜቦ ገልጸዋል ። በአጠቃላይ የተቋማት የመረጃ ስርዓት በዲጂታላይዘሽን ስራዎች ለማሻሻል እና ለማስተዳደር ምቹ እንዲሆን የተደረጉ ስራዎች አዎንታዊ ውጤቶችን እያስመዘገቡ መሆኑ ገልጸው ቀጣይም የተሰጡት ግብዓቶች ተስተካክሎ ሆስት ከተደረገ ቦኃላ የአጠቀቀምና አስተዳደር ቴክኒካል ስልጠና እንደምሰጥ አቅጣጫ ተመላክቷል።