
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የድረ ገፅ ማስተዳደርና የሳይበር ደህንነት ቴክኒካል ስልጠና ለክልሉ ፍትህ ቢሮ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ። የካቲት 13/2017 ዓ.ም ቢሮው ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የድረ-ገጽ ልማት ስራን በማጠናቀቅ በዶሜይን ስሙ https://www.cerjustice.gov.et/ አየር ላይ መዋሉን(Host) አስመልክቶ ከፍተኛ የሶፍትዌር ባለሙያ በሆኑት በአቶ መንሱር ሀምዛ ስለ ዌብ ሳይት አስተዳደርና ሳይበር ደህንነት ስልጠና ለቢሮው የስራ ክፍል ኃላፊዎች አጠቃላይ ገለፃ እና በተለይም ድረ-ገጹን በቀጣይ ለሚያስተዳድሩ የኢኮቴ እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የማስተዳደርና የሳይበር ደህንነት ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው የቢሮ ም/ኃላፊ እና የወንጀልና የፍትሐብሔር ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ገብሬ አስፋው የመክፍቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን በንግግራቸውም የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በፈቃደኝነትና በተነሳሽነት ለተደረገልን የተቋሙ ድረ-ገጽ የማበልፀግ እና ባለሙያዎችን የማስልጠን ስራ በቢሮው ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። በመቀጠልም ስልጠናው በተግባር የተደገፈ ድረ ገፅ የማስተዳድርና የሳይበር ደህንነት ዙሪያ ሰፊ ገለፃ እና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ከሰልጣኞቹም የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።