Skip to main content
zena27

ቢሮው ለሳይበር ጥቃት ምላሽ መስጠት የሚችል የሰው ሃይል ለማፍራት እየሰራ መሆኑን ገለጸ። ለሳይበር ጥቃት ምላሽ መስጠት የሚችል የሰው ሃይል ለማፍራት እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለጸ ቢሮው ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመተባበር ስለ ሳይበር ስፔስ ምንነት፣ ስለተሻሻለው የሳይበር ፓሊሲና ስታንዳርዶች ለባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል። የቢሮው ምክትልና የኢኮቴ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ ስልጠናው የኢኮቴ መሠረተ ልማት ሲለማ ሊታሰብ ሲለሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች እና በሀገርና በግለሰቦች ደህንነት ላይ ሊደርስ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅም ያጎለብታል ብለዋል። የዲጅታል ዓለም ላይ እንደመሆናችን ስለ ሳይበር ስፔስ ምንነትና ተያይዘው ስለሚመጡ ጉዳዮች ማወቅና በትብብር መስራት ይጠበቃል ያሉት ኃላፊው ለዚህም ቢሮው ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ ለሳይበር ጥቃት ምላሽ መስጠት የሚችል የሰው ሃይል ለማፍራት እንዲያስችል ቢሮው ለተቋሙ ሰራተኞችና ለባለድርሻ ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና የመስጠት ስራ ይሰራል ብለዋል። እንደ ሀገር ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው በክልሉም ለዚህ አጋዥ የሚሆኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተተገበሩ መሆኑን አስረድተዋል።