Skip to main content
zena24

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እንደ ተቋም የመረጃ ስርዓቱን ለማዘመን እና ጊዜውን የዋጀ መረጃን ለማደራጀት ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመቀናጀት ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል። ጥር፦27/2017 ከእነዚህ ስራዎች ውስጥ በዋናነት በሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በዛሬው ዕለት በወራቤ ከተማ በጋራ ግምገማ አድርጎል። ውይይት የተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል የዳታቤዝ/ሲስተም/ እና ዌብሳይት ሲሆን ተቋሙ የዳታቤዝ ስርዓቱን እና ዌብሳይቱን ለማልማት የተሻለ አስተዋፅዖ እንዳለው እና በዚህ ሂደት ውስጥ የተቋሙ የመረጃ ስርዓት የበለጠ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን። በተጨማሪም የቱሪስት ፍሰትን ለማስተዳደር የቱር ጋይድ ማፕ ስራ ተቋሙ የቱሪስት ፍሰትን በቀላል እና ዘመናዊ መንገድ ለማስተዳደር የቱር ጋይድ ማፕ ስራን ያለበትን ደረጃ መመልከት የተቻለ ሲሆን ይህ ስራ ቱሪስቶች በቀላሉ መረጃን ማግኘት እና አገልግሎቶችን ለመጠቀም የሚያስችላቸው መሆኑ ተገልጿል። በውይይት መድረኩ ተቋሙን የአሁኑን ደረጃ በትክክል ለመለየት እና የወደፊት እቅዶችን በተለይም የቱሪዝም እና የባህል መረጃዎችን በተመለከተ የበለጠ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ስርዓቶችን ለማምጣት የሚያስችሉ ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ባህል ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ ገልፀዋል። በአጠቃላይ የተቋሙ የመረጃ ስርዓት ማሻሻያ እና የቱሪስት ፍሰትን ለማስተዳደር የተደረጉ ስራዎች አዎንታዊ ውጤቶችን እያስመዘገቡ መሆኑ ተመላክቷል።