Skip to main content
zena22

በዕቅድ ክንውን በጥንካሬ የተለዩትን አጠናክሮ በማስቀጣል፣ ጉድለቶችን በቀጣይ በመቅረፍ ለህዝብ ተጠቃሚነት መስራት እንደሚገባ ተመላከተ።  የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተላቸውን ተቋማት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በወልቂጤ ከተማ እየገመገመ ይገኛል።

ቋሚ ኮሚቴው በትናንትና ውሎው የትምህርት፣ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ፣ ሰራተኛና ማህበራዊ፣ እንዲሁም አመራር አካዳሚ ተቋማት ዕቅድ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን በዛሬው ውሎው የጤና፣ ባህልና ቱሪዝም፣ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተቋማት ዕቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል።

የግምገማ መድረኩ በምክር ቤቱ የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራ የተመራ ሲሆን፣ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የተቋማት የስራ ኃላፊዎችና የማኔጅመንት በተገኙበት አፈፃፀሙ ተገምግሟል። በመድረኩ የተቋማቱ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ፣ በቋሚ ኮሚቴው ተገምግሞ ግብረ መልስ ተሰጥቶበታል። በግብረ መልሱም፣ በዕቅድ ክንውን በጥንካሬ የተለዩትን አጠናክሮ በማስቀጠል፣ በጉድለት የተለዩት ላይ ደግሞ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተመላክቷል። የቋሚ ኮሚቴው የግምገማ መድረክ ነገም የሚቀጥል ይሆናል።