Skip to main content
zena18

የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የአሰራር ስርዓት ለመፍጠር የሚያስችሉ መመሪያዎችን ማጽደቅ ቻለ። ቢሮው የአሰራር ስርዓት ለመትከል እና ተቋም ለመፍጠር የሚያስችሉ የተለያዩ 6 መመሪያዎች ከክልሉ ፍትህ ቢሮ ጋር በመናበብ ማጽደቅ ተችሏል። እነዚህም:- 1; የኢኮቴ መሳሪያዎች፣ አገልግሎቶችና መሰረተ ልማት አቅርቦት አፈጻጸም መመሪያ፣ 2; የማህበረሰብ መረጃ ማዕከላት የአደረጃጀትና የአስተዳደር የአሰራር መመሪያ 3; የሳይንስ ካፌዎች የአደረጃጀትና አስተዳደር የአሰራር መመሪያ፣ 4; የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ማበረታቻና ሽልማት አሠጣጥ የአሠራር መመሪያ፣ 5; የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበባት አደረጃጀትና ፕሮጀክቶች ድጋፍ አሠጣጥ የአሰራር መመሪያ፣ 6; ችግር ፈቺ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ድጋፍ አሠጣጥ የአሠራር መመሪያዎች ናቸው። ሙሉ የመመሪያውን መረጃ ለማግኘት በተቋሙ :- ዌብሳይት:- https://cebosit.gov.et ቴሌግራም:- Central Ethiopia Regional State Science & Information Technology Bureau ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።