Skip to main content
zena16

ምርምርና ጥናት በማድረግና ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎችን ደግፎ በማጎልበት ውጤታማ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስርዓት መዘርጋት የሚያስችል ውይይት ተካሔደ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የሳይንስ ቴክኖሎጂ ምርምርና ጥናት በማካሄድ እንዲሁም ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎችን ደግፎ በማጎልበት ቴክኖሎጂያዊ መፍትሔ በዘላቂነት ለማቅረብ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን የቢሮ ምክትል ኋላፊ አቶ ሙሂዲን ሁሴን ገልጸው በክልላችን የወተት ምርትና ምርታማነትን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለማሳደግ የሚያስችል ፕሮጀክት የኢፌድሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር; የዋቻሞ ዩንቨርስቲ እና የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በጋራ የሚተገብሩት ፕሮጀክት ነው። በዩንቨርስቲው እና በቢሯችን የተመራማሪዎች ቡድን አባላት ያቀረቡትን የወተት ምርትና ምርታማነት ፕሮጀክት በጋራ በመገምገም የግብዓት ሀሳቦች መስጠት ተችሏል። ዶ/ር ሳራ ሽኩር በዋቻሞ ዩንቨርስቲ አካዳሚክና ምርምር ዘርፍ ምክትል ፕረዚዳንት ፕሮጀክቱ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ የሚያሳድግ; የስራ ዕድል የሚፈጥር እንዲሁም ለተጠቃሚው ማህበረሰብ የወተት ተዋጽኦን ለማቅረብ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን አንስተዋል። በተጨማሪም በክልሉ የግብርና ሴክተር በተለዩ ቴክኒካል ችግሮች መነሻነት የተለዩ ቴክኖሎጂዎችን በውስጥ አቅም አምርቶ ለማሸጋገር መግባባት የተቻለ ሲሆን በቀጣይ የተባባሪ መስሪያ ቤቶች ኃላፊዎች በተገኙበት ወደ ትግበራ የሚገባ ሲሆን ተጨባጭ ውጤት በሚያመጣ ሁኔታ እንደሚሠራ ከስምምነት መድረስ ተችሏል።