
ኮዲንግ ማለት የዛሬ ፕሮግራም ብቻ ሳይሆን የነገም ጭምር መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ ገለጹ። የቢሮው ዋና ኃላፊ ይህን ያሉት ከፌዴራል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር መስሪያ ቤት የተውጣጣ ቡድን ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ድጋፍ እና ክትትል ባደረገበት ወቅት ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ ለፌደራል ድጋፍና ክትትል ቡድኑ በባለፉት ወራት በተቋሙ በተከናወኑና እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ላይ እንዲሁም ተቋሙ ውጤታማነትን መሰረት ያደረገ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል። ይህ ፕሮግራም ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ወደ ትግበራ ሲገቡ ሁሉም በክልላችን የሚገኙ አመራሮች በተገኙበት ግንዛቤ መፍጠር መቻላቸውን ያነሱት ዋና ኃላፊው ከዚህ በተጨማሪም ይበልጥ ለማጠናከር ከሚዲያ አካለት በጋራ እያሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በሁሉም በክልሉ ቢሮዎች ስለ ኢትዮ ኮደርስ ግንዘቤ መፈጠሩን ያነሱት አቶ ሰላሙ ይህ የሚያሳየው የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ያደረገው ጠንካራ እንቅስቃሴ ማሳያ መሆኑን አስገንዝበዋል። በጠቅላይ ሚኒስተራችን የተጀመረውን የ5 ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ ኢኒሼቲቭ እንደ ክልልም በርካታ ዜጎች ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸውን እየጎለ መምጣቱን አንስተዋል። በአጠቃላይ እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ50 ሺህ በላይ ህብረተሰብ የኢቲዮ ኮደርስ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑና በበጀት አመቱም ከ28 ሺ በለይ ተሳታፊዎች በስልጠናው ተሳትፈዋል ያሉት አቶ ሰላሙ ከ8 ሺ በለይ የሚሆኑት ሰርቲፊኬት መውሰድ መቻላቸውንም ገልጸዋል። ይህን ተግባር ሲያከናውን ምንም እንኳ ብዙ ምቹ ሁኔታዎች ቢኖሩም አንዳንድ ተግዳሮቶች በመኖራቸው የፌደራል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂን ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካለት ድጋፍ መድረግ እንደሚኖርባቸው ያነሱት ኃላፊው ቢሮው የተገኙ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል የተሻለ ለመስራት ማቀዱንም ተናግረዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ ቢሮው ሁሉንም የሚዲያ አማራጮችና ዙም በመጠቀም እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ የዙም አማራጮችን በመጠቀም ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበበት እንደሚገኝ አንስተዋል። የፌደራል ኢኖቬሽን ባለስልጣን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ዲቨሎፕመንት ዲጂታል እንዱስትሪ ዴስክ ማናጀር አቶ ምንዳ ፈለቃ በመድረኩ ለቢሮው ማኔጅመንት አካላት ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎችም የቢሮሩ ሃለፊና ባለሙያዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውበታል። የቢሮው የማኔጅመንት አካለት እስካሁን ባለው ቢሮው ኢትዮ-ኮደርስን በተመለከተ እየሰራ ያለውን ስራ መመሪያ ከመስጠት ባለፈ በአካል በመሄድም ጭምር ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እያሰሩ መሆኑን በማንሳት በዚህም አበረታች ለውጦች እያመጡ መሆኑንም ገልጸዋል።