ክልሉን የሳይንስ፣ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ማዕከል የማድረግ ግብ ለማሳካት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለጸ። (ወራቤ፣ ጥር 21/2017 ዓ/ም) ቢሮው በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈጻጸም እና በቀጣይ ወራት ዕቅድ ዙሪያ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ መክፈቻ የቢሮው ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ እንደተናገሩት ቢሮው ክልሉን የሳይንስ፣ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ…
የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እና ውጥኖች ላይ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽንና አውደ ጥናት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም በክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሰገን ጥሩነህን ተከፍቷል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና በኢትዮ ቴሌኮም የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እና ውጥኖች ኤግዚቢሽንና አውደ ጥናት በአዲስ አበባ…
የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የአሰራር ስርዓት ለመፍጠር የሚያስችሉ መመሪያዎችን ማጽደቅ ቻለ። ቢሮው የአሰራር ስርዓት ለመትከል እና ተቋም ለመፍጠር የሚያስችሉ የተለያዩ 6 መመሪያዎች ከክልሉ ፍትህ ቢሮ ጋር በመናበብ ማጽደቅ ተችሏል። እነዚህም:- 1; የኢኮቴ መሳሪያዎች፣ አገልግሎቶችና መሰረተ ልማት አቅርቦት አፈጻጸም መመሪያ፣ 2; የማህበረሰብ መረጃ ማዕከላት የአደረጃጀትና የአስተዳደር የአሰራር መመሪያ 3; የሳይንስ ካፌዎች የአደረጃጀትና አስተዳደር…
የወራቤ ክላስተር የመሠረታዊ ፓርቲ ድርጅት አባላት ኮንፍራስ እየተካሄደ ነው ጥር 8/2017 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወራቤ ክላስተር የመሠረታዊ ፓርቲ ድርጅት አባላት ኮንፍራስ እየተካሄደ ነው። ኮንፍረንሱ 2ኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤን ለማካሄድ የሚደረግ ሂደት አካል ነው ተብሏል። በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱን ጨምሮ የወራቤ ክላስተር…
ምርምርና ጥናት በማድረግና ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎችን ደግፎ በማጎልበት ውጤታማ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስርዓት መዘርጋት የሚያስችል ውይይት ተካሔደ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የሳይንስ ቴክኖሎጂ ምርምርና ጥናት በማካሄድ እንዲሁም ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎችን ደግፎ በማጎልበት ቴክኖሎጂያዊ መፍትሔ በዘላቂነት ለማቅረብ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን የቢሮ ምክትል ኋላፊ አቶ ሙሂዲን ሁሴን ገልጸው በክልላችን…
አቶ ሠላሙ አማዶ ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኋላፊ አቶ ሠላሙ አማዶ የገና በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አቶ ሠላሙ ባስተላለፉት መልዕክት "ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ" ብለዋል። በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የጤና ተቋማት ስርጭት በጂኦስፓሻል ሳይንሳዊ ጥናት ማድረጉ ተሰማ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በጋራ በቅንጅት የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።
ኮዲንግ ማለት የዛሬ ፕሮግራም ብቻ ሳይሆን የነገም ጭምር መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ ገለጹ። የቢሮው ዋና ኃላፊ ይህን ያሉት ከፌዴራል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር መስሪያ ቤት የተውጣጣ ቡድን ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ድጋፍ እና ክትትል ባደረገበት ወቅት ነው።
የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ፍትሀዊ ውድድርን በማስፈን ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በአዕምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃ ዙሪያ ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ እየተሰጠ ነው። ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የቢሮው ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ እንደገለጹት የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነትን ማረጋገጥ የፈጠራ…
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስካሁን 23 ሺህ ገደማ ሰልጣኞች የኮዲንግ ሥልጠና መሰልጠናቸው ተገለጸ። (ሆሳዕና፣ ታህሳስ 16/2017) ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ በጉራጌ ዞን የኮዲንግ ሥልጠና ሂደትን ምልከታ አድርገዋል። የኮዲንግ ሥልጠና በሀገር ደረጃ 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የሚሰለጥኑበት ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ መሆኑን በማስታወስ፤ በክልል ደረጃ በሶስት አመት ውስጥ ከ198 ሺህ በላይ…