Cebosit
Tue, 01/10/2023 - 02:53

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ በዚህ ወቅት እንደገለፁት በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የክልሉ መንግስት የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ የ100 ቀናት እቅድ አዘጋጅቶ ተግባራዊ እያደረገ ስለመሆኑ አቶ አንተነህ ጠቁመዋል።
በትምህርት፣በጤና እና በሴቶችና ህፃናት ፣በፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አብራርተዋል።
በክልሉ በማህበራዊ ክላስተር ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን የ5ወር አፈፃፀም እና የ100 ቀን እቅድ አፈፃፀም የቢሮ ኃላፊዎች አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
ምንጭ የስልጤ ዞን የመንግት ኮሙኒኬሽን