Skip to main content
news6

የሳይንስና ፈጠራ ክበባት በትምህርት ቤቶች በልዩ ሁኔታ በመደገፍ በሃገር ደረጃ ተወዳዳሪ የአካባቢው ገፅታ መቀየር የሚችሉ የፈጠራ ስራ ባለቤቶች ማፍራት እንደሚቻል የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ገለጸ፡፡

መምሪያው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራና ስርፀት ዘርፍ ስራዎች ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በቡታጅራ ከተማ ማዕከል ለወረዳና ከተማ አስተዳደር አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘነበ መዶ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የስልጠናው መርሃ ግብር አስጀምረዋል። ስልጠናው መዋቅሮች በሳይንስና ፈጠራ ዘርፉ በማህበራዊ በኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ያለው ጠቀሜታ ተገንዝበው በተገቢው መተግበር እንዲችሉ ያግዛል ሲሉ ኃላፊ ተናግረዋል። የፈጠራ ባለቤት የሆኑ አካላት በማነቃቃት በፈጠራ ስራቸው ተጠቅመው ማህበረሰብን ተጠቃሚ በማድረግ እንደሀገር የተጣለው ግብ ለማሳካት የሚችሉበት አግባብ ለመፍጠር ስልጠናው ዓላማ በማድረግና እንደተዘጋጀ ገልፀዋል። የሳይንስና ፈጠራ ክበባት በልዩ ሁኔታ በትምህርት ቤቶች ደረጃ በማጠናከር ህፃናት ወጣቶች ነገ ትላልቅ በመድረስ በሀገር ደረጃ ተወዳደሪ ከመሆንም ባለፈዉ የአካባቢው ገፅታን መቀየር የሚችሉ የፈጠራ ባለቤቶች መፍጠር እንዲችሉ ይረዳል ብለዋል። አመራርና ባለሙያው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉት በመገንዘብ በቴክኖሎጂ የተወዳዳሪነት አቅማቸውን እንደሚያሳድግ በመረዳት ተቋሙ መደገፍ አግባብ የሚፈጥር ይሆናል የግሉ ዘርፍ የፈጠራቸውን ባለቤቶችንን በልዩ ሁኔታ መደገፍ የሚቻልበት ሁኔታን መከተል እንደሚገባ ያነሱት ኃላፊው በስልጠናው ተገቢው የእውቅና አሰጣጥ ፣የድጋፍና የአምሮ ጥበቃ ላይ ያተኩሩ ጠቃሚ ስልጠናዎች እንዳገኙ አንስተዋል። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የሳይንስና ፈጠራ አቅም ግንባታ ዋና ስራ ሂደት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ወንድሙ ጀንቦ በበኩላቸው ችግር ፈች የሆኑ ፈጠራ ስራዎች ተፈጥረው ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉበት አግባብ መፍጠር ዓላማ ማድረጉ አንስተዋል። በሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ በሃሳብ ደረጃ ያሉ ነገሮችን ወደተግባር ቀይሮ ተጠቀሚ ማድረግ ይገባል ሲሉ አንስተዋል። እንደሃገር በፈጠራና ኢኖቬሽን ዘርፍ በርካታ ያልተሰሩ ተግባራት መኖራቸውን በቀጣዩ ትውልድ በሃሳብ ደረጃ አመንጭተው ወደተግባር እንዲቀይሩ ተከታታይ የሆነ ድጋፍ በማድረግ የየፈጠራጠራ ስራዎች ወጥተው የሚያደርጉበት እንደሚፈጥር ገልፀዋል። ተቋሙ ውጤታማ ስራን በመስራት የፈጠራ ስራዎች ሽግግር እንዲያደርጉ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ አመላክተዋል። የፈጠራ ስራዎቻቸው እውቅና በየደረጃው በማሰጠት የአዕምሮ ጥበቃና ህጋዊ ከለላ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ቡድን መሪው አንስተዋል።