የቢሮዉ ኃላፊ መልዕክት

message

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሳይንስና ኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ ቢሮ

                       አቶ ሰላሙ አመዶ ዋጨንጎ የቢሮው ሀላፊ መልዕክት                  

የቢሮው ሀላፊ መልዕክት

ሳይንስና ኢንፎርመሽን ቴክኖሎጂ   ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት የሚያበረክተው  አስተዋጽኦ ከምንም በላይ መሆኑን ዛሬ ላይ የስልጣኔ ጫፍ የደረሱ፣ የበለፀጉና የዓለማችን ሃያላን ተብለው የሚጠሩ አገሮች ምሥክሮች ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ መንግስት የሀገራችን ሕዝብ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆንና የቴክኖሎጂው ሽግግር ከጫፍ እንዲደርስ ተግቶ በመሥራቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀላል የማይባል የሀገራችን ሕዝብ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን ችሏል፡፡  ለዚህም ማሳያ መሆን የሚችሉ በርካታ ተግባራትን መጥቀስ የሚቻል ሲሆን በክልላችን የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከሚመለከታቸው /ቤቶች ጋር በመሆን በአያሌ የገጠር ቀበሌያትና ወረዳዎች የገጠሩ ሕብረተሰብ ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ከሌሎች የመረጃ ምንጮች የሚፈልጓቸውን መረጃዎች በተለያዩ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች አማካይነት ማግኘት እንዲችሉ የማህበረሰብ መረጃ ማዕከላትን አቋቁሞ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡  ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሽቦ አልባ ስልኮችም በብዙ የገጠር ቀበሌያት በቢሮውና አግባብነት ባላቸው ተቋማት በኩል የተሠራጩ ሲሆን እስኩል ኔትና ወረዳ ኔቶችም እንዲሁ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  በክልል ማዕከል፣ በዞኖች፤ በልዩ ወረዳዎች፤ በወረዳዎችና በከተማ አስተዳደሮች የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ  መሠረተ ልማት ደረጃ በደረጃ እየተዘረጋ ያለ ሲሆን በዋናነት የመንግስት መረጃ ሥርዓት  የማሳለጥ፣ የቪዲዮ ኮንፍረንስ አገልግሎት በመስጠት ፈጣን የሆነ መረጃ እንዲዳረስ የማድረግና የማህበረሰብ መረጃና ሬድዮ አገልግሎት በመስጠት በርካታ ወጣቶችን በማደራጀትና በማሰልጠን ወደ ስራ እያስገባ ይገኛል፡፡ ባለፉት ዓመታት በኢኮቴ ዘርፍ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ተመራቂዎችን በማህበር በማደራጀት የተለያዩ ድጋፎችን ማለትም ስልጠና፣ የገበያ ማፈላለግና የማማከር አገልግሎት በመስጠት የግል ካምፓኒ ፈጥረው  ወደ ንግድ ዓለም እንዲገቡ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቢሮውን ዌብ ሳይት በማልማት እና የፌስቡክ ገጽ በመክፈት እንዲሁም የተለያዩ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በተቋማችን አጠቃላይ አፈጻጸምና ሁኔታ ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እተከናወነ ይገኛል፡፡

ወቅታዊ ዜናዎች

zena87

ተረጋገጡና ተዓማኒነት ያላቸው ክልላዊ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል የመረጃ ቋት ይፋ ተደረገ።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕላን ልማት ቢሮ ከክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመሆን የለማ የተቀናጀ መረጃ ማሰራጫ ዌብ-ሳይት ርክብክብ ተደርጓል።…

zena86

በቴክኖሎጂ የታገዘና በዲጂታል ዕውቀት ላይ የተመሰረተ ብዝሃ ኢኮኖሚ የመገንባት ተልዕኮን ለማሳካት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ድርሻ ጉልህ ነው- የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ (ሆሳዕና፣ ጥር 18/2018)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር…

zena85

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ186 ሺህ በላይ ዜጎች የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠናን ተከታተሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ186 ሺህ በላይ ሰዎች የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና መከታተላቸውን የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ ሰላሙ አማዶ ለጋዜጣ…

zena84

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ ከክልሉ ሳይንስ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር ያስለማዉን የተቋሙን ዌብ ሳይት ተረክቧል፡፡ በርክክቡ ወቅት የቢሮዉ ሃላፊ የተከበሩ አቶ ገብሬ ጋጌ ባስተላለፉት መልዕክት ዌብ ሳይቱን በማልማት ላቀረበዉ የክልሉ ሳይንስ…

zena82

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ። ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል። የመግባቢያ ሰነድ የመፈራረም…

zena83

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከባለሙያዎችና ከሠራተኞች ጋር የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመ።‎ታህሳስ 27/2018 ዓ/ም ‎ ‎​የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ፤ ችግር ፈቺ የምርምርና የቴክኖሎጂ ፈጠራ…

ተልዕኮ

ለክልሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለህብረተሰቡ በአግባቡ በማልማት፣ በመተግበርና በማስፋት ክልላዊ ብሎም አገራዊ የተወዳዳሪነት አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ነዉ፡፡

ራዕይ

“በ2030 በክልላችን ውጤታማ የሆኑ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመማር፣ የማልማት፤ የመፍጠር፣ የማላመድ እና የመጠቀም አቅም ተገንብቶ ማየት”      

እሴቶች

በጎ ህሊናና ቅን ልቦና፣

የስራ ፍቅርና ትጋት፣

ያልተገደበ አስተሳሰብና ምናባዊ ጉዞ፣

ለለውጥ በጋራ መስራት፤

ውጤታችንም ሆነ ውድቀታችን የጋራችን ነው፤

ችግር ፈቺነት፤

የማይረካ የመማር ጥማት፤

ለትውልድ የሚተላለፍ መሠረት፣

ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራርና ቀጣይነት ያለው መሻሻል፣